ba
የእግዚአብሔር ቃል   

                                                                             

                                 የተወደዳችሁ ምእመናን
 ልጆቻችሁ ከመዝሙር ጋር ሃይማኖታቸውን፣ ሥነምግባራቸውን እንዲማሩ ያስፈልጋል፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትመጡ ልጆቻችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡ ብቻችሁን ከመጣችሁ የምትሠሩትን አያውቁም፤ ወዴት እንደሔዳችሁ አያውቁም፡፡ ወራሾቻችሁ አይሆኑም፡፡ አሳዩአቸው፡፡ ሥዕሉን ይሳሙ፤ ቅዳሴ ጠበል ይጠጡ፡፡ በእምነቱ አሻሹአቸው፤ መስቀል እንዲስሙ አስተምሯቸው፡፡
የሚታጠነውን ዕጣኑን ያሸትቱ፤ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ይቀበሉ፤ ቃጭሉ፣ ደወሉ ሲደወል ይስሙ፤ ቄሳቸው ማን እንደሆነ፣ቤተ ክርስቲያን ምን እንደሆነች፣ በውስጧ ምን ምን እንደሚሠራ ያጥኑ፤ ይማሩ፡፡ ወደ ሰንበቴም ስትሔዱ ይዛችኋቸው ግቡ፤እነርሱም ነገ ይህን እንዲወርሱ፤ የነገ ባለአደራዎች መሆናቸውን እንዲያውቁ ይማሩ፡፡ ማኅበሩ፣ ዝክሩ፣ ሰንበቴው፣ በቅዱሳን ስም በበዓልመሰብሰቡ፣ ማስቀደሱ፣ መቁረቡ፣ ቅዳሴ ጠበል መጠጣቱ፣ መስቀል መሳለሙ..... አባቶቻችንና እናቶቻችን ሥርዓታችንን እምነታችንን ሁሉ ሰፍረው ቆጥረው አስረክበውናል፡፡ እና ይህ ትውልድ ይህንን እንዳያጣ ነው
አደራ የምንለው፡፡ ይህ ትውልድ ይህንን ከቀበረ በኋላ፣ ይህንን ካጠፋ በኋላ... ሃይማኖቱን ፍለጋ፣ ታሪኩን ፍለጋ ወደ ቤተ መዘክር እንዳይሔድ ነው፡፡ ስለዚህ እምነታችሁን፣ ሥርዓታችሁንና መንፈሳዊ ውርሳችሁን እንድትጠብቁ አደራዬ የጠበቀ ነው፡፡
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ የሸዋ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ 

/1932 ዓ.ም - 1982 ዓ.ም./ በሻሸመኔ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን
ሚያዝያ 23 ቀን 1982 ዓ.ም ተገኝተው ለምእመናን ከሰጡት ትምህርት የተወሰደ ነው፡፡
 ልጆች አበባዎች ናቸው፡፡ ክብካቤ ክትትል የማይለያቸው፤ እንደ አዲስ ተክል በአግባቡ መኮትኮት፣ ማረምና የሚያስፈልጋቸውን ማሟላት የግድ ነው፡፡ ሕፃናትን ፍላጐታቸውን በማጤን በሃይማኖት፣ በመልካም ትምህርትና ሥነ ምግባር ኮትኩቶ በቀናው መንገድ መምራት ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡ የነገይቷን ቤተ ክርስቲያን ተረካቢና አገልጋይ፣ሃገረ ገምቢ ብቁ ዜጋ፣ መልካም ፍሬ ናቸውና፡፡

 

 

አርባ ሁለቱ ህፃናት














ተጨማሪ ቪዲዮ