ኦሪት ዘዳግም |
8፥20 |
የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል
ስላልሰማችሁ እግዚአብሔር ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው እንደ አሕዛብ እንዲሁ እናንተ ትጠፋላችሁ። |
10፥8 |
በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል
ኪዳን ታቦት ይሸከም ዘንድ፥ እርሱንም ለማገልገል በእግዚአብሔር ፊት ይቆም ዘንድ፥ በስሙም ይባርክ ዘንድ
እግዚአብሔር እስከ ዛሬ ድረስ የሌዊን ነገድ ለየ። |
13፥17-18 |
ዛሬም እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ
ትጠብቅ ዘንድ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ የሚያሰኘውን ታደርግ ዘንድ የአምላክህን የእግዚአብሔርን
ቃል ስትሰማ፥ የእግዚአብሔር
መቅሠፍት ቍጣ ይመለስ ዘንድ፥ ለአባቶችህም እንደ ማለላቸው ይምርህ ዘንድ፥ ይራራልህም ዘንድ፥ ያበዛህም ዘንድ፥
እርም ከሆነው አንዳች ነገር በእጅህ አይንጠልጠልብህ። |
15፥4-5 |
አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ
ርስት አድርጎ በሰጠህ ምድር ላይ እግዚአብሔር በእውነት ይባርክሃልና አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል
ፈጽመህ ብትሰማ፥ ታደርጋትም ዘንድ ዛሬ የማዝዝህን ይህችን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቅ፥ በመካከልህ ድሀ አይኖርም። |
26፥14 |
በኀዘኔ ጊዜ እኔ ከእርሱ አልበላሁም፥
ለርኵስነቴም ከእርሱ አላወጣሁም፥ ከእርሱም አንዳች ለሞተ ሰው አልሰጠሁም የአምላኬንም የእግዚአብሔርን ቃል
ሰምቼአለሁ፥ ያዘዝኸኝንም ሁሉ አድርጌአለሁ። |
28፥1 |
እንዲህም ይሆናል የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል
ብትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ሁሉ ብታደርግ ብትጠብቅም አምላክህ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ
ከፍ ያደርግሃል። |
28፥2 |
የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል
ብትሰማ እነዚህ በረከቶች ሁሉ ይመጡልሃል ያገኙህማል። |
28፥15 |
ነገር ግን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል
ባትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ ባትጠብቅ ባታደርግም፥ እነዚህ መርገሞች ሁሉ ይመጡብሃል
ያገኙህማል። |
28፥45 |
የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል
ስላልሰማህ፥ ያዘዘህንም ትእዛዙንና ሥርዓቱን ስላልጠበቅህ፥ እስክትጠፋ ድረስ እነዚህ መርገሞች ሁሉ ይወርዱብሃል፥
ያሳድዱህማል፥ ያገኙሁማል። |
28፥62 |
የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል
አልሰማችሁምና ከብዛታችሁ የተነሣ እንደ ሰማይ ከዋክብት የነበረው ቍጥራችሁ ጥቂት ሆኖ ይቀራል። |
30፥8 |
አንተም ተመልሰህ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል
ትሰማለህ፥ ዛሬም እኔ የማዝዝህን ትእዛዙን ሁሉ ታደርጋለህ። |
30፥9-10 |
የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል
ብትሰማ፥ በዚህም ሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ብትጠብቅ፥ በፍጹምም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ ወደ
አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ብትመለስ፥ እግዚአብሔር በአባቶችህ ደስ እንዳለው በመልካሙ ነገር ሁሉ እንደ ገና
በአንተ ደስ ይለዋልና አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ በሆድህም ፍሬ በከብትህም ፍሬ በእርሻህም ፍሬ እጅግ
ይባርክሃል። |
31፥9 |
ሙሴም ይህችን ሕግ ጻፈ፥ የእግዚአብሔርንም የቃል
ኪዳኑን ታቦት ይሸከሙ ለነበሩት ለሌዊ ልጆች ለካህናቱ ለእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ ሰጣት። |
31፥25 |
ሙሴ የእግዚአብሔርን
ቃል ኪዳን ታቦት
የሚሸከሙትን ሌዋውያንን እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ |
34፥5 |
የእግዚአብሔር
ባሪያም ሙሴ እንደ እግዚአብሔር ቃል በዚያ
በሞዓብ ምድር ሞተ። |