| |
አገር በታሪክ በቋንቋ በሀይማኖት
በልምድ በተስፋ በደስታና በመክራ ተሳስሮ የሚኖር አንድ ወገን የሆነ ሕዝብ የሚኖርበት የዓለም ክፍል ነው ። አገር
ማለት አያት ቅድም አያት የተወለዱበት አድገውም በጀግንነት ከውጭ ጠላት እየተከላከሉ ለሕዝብና ለመንግሥት የሚጠቅም
ሥራ ሠርተው እድሜያቸው ሲደርስም ልጆቻችውን ተክተው የተቀበሩበት ጉድጓድ ነው ።በመወለድ እትብት በመሞት አካል
ከአፈሩ ጋራ ስለ ሚዋሐዱ የአገሩ አፈር ሕዝብ በላዩ የሚኖርበት ማለት ነው ።እግዚአብሔር ከምድርዋ ፍሬ ሕይወት
እንዲጋኝባት በማድረጉ አገር እያጠባች የምታሳድግ ፍቅርዋ በአጥንትና በሥጋ ገብቶ የማይደመሰስ የሆነች እናት ማለት
ነው። ከልጅነት ጀምሮ ወንዙን ተራራውን ሜዳውን ቆላውንና ደጋውን በማየት ስለምታሳደግ ፥አባቶች በሕህወትና በሞት
የሥሩበት ደግ ሥራ በአእምሮ ታትሞ ስለ ቀረ በአገር እስካሉ ሲታይ በስደት ሲሆኑ ሲታሰብ ፍቅርና ናፍቆት
የሚያሳድር አገር ነው። አገር አባት እናት ዘመድ ምግብ ጌጥና ሀብት በመሆኑ ድኅነትና ጥቃት በመጣ ቁጥር እስከ
ሞት ድረስ እንዲሠራበት ከአያት ከቅድም አያትና ከአባቶች በጥብቅ የተሰጠ ያደራ ገንዘብ ነው
ከታሪክና ምሳሌ (3 ኛ ምጽሐፍ
| |
|
Unable to read the
text?
download N V
and copy to the
Directory c:/windows/font/ | | |