ማውጫ

xx
ቅድመ ገጽ
መልእክት
ተግባራት
ጥቅሶች
ድረገጾች

ቃል 

 
  micael    
banner       
  mariam

 











        



                           ኢ ት ዮ ጵ ያ  በ መ ጽ ሐ ፍ   ቅ ዱ ስ                                        

መጽሐፍ

ምዕራፍ

ቁጥር

 

ኦሪት ዘፍጥረት

2

13

የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው እርሱም ኢትዮጵያ ምድር ሁሉ ይከብባል።

ኦሪት ዘኍልቍ

12

1

ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ባገባት ኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ
ላይ ተናገሩ።

መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ

19

9

እርሱም፦ ኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊወጋህ መጥቶአል የሚል ወሬ በሰማ ጊዜ ደግሞ ወደ
ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፥ እንዲህ ሲል፦

መጽሐፈ ዜና

መዋዕል ካልዕ

12

3

ከእርሱም ጋር ከግብጽ ለመጣው ሕዝብ ቍጥር አልነበረውም እነርሱም የልብያ ሰዎች፥
ሱካውያን፥ ኢትዮጵያ ሰዎችም ነበሩ።

 

14

9

ኢትዮጵያዊውም ዝሪ አንድ ሚሊዮን ሰዎችና ሦስት መቶ ሰረገሎች ይዞ ወጣባቸው ወደ መሪሳም
መጣ።

 

14

12

እግዚአብሔርም በአሳና በይሁዳ ፊት ኢትዮጵያውያንን መታ ኢትዮጵያውያንም ሸሹ።

 

14

13

አሳም ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዱአቸው ኢትዮጵያውያንም ፈጽመው
እስኪጠፉ ድረስ ወደቁ፥ በእግዚአብሔርና በሠራዊቱ ፊት ተሰባብረዋልና እጅግም ብዙ ምርኮ ወሰዱ።

 

16

8

ኢትዮጵያውያንና የልብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረገሎችና ፈረሰኞች የነበሩአቸው እጅግ ታላቅ
ጭፍራ አልነበሩምን? በእግዚአብሔር ስለ ታመንህ በእጅህ አሳልፎ ሰጣቸው፥

 

21

16

እግዚአብሔርን የፍልስጥኤማውያንና ኢትዮጵያውያን አጠገብ የሚኖሩትን የዓረባውያንን
መንፈስ በኢዮራም ላይ አስነሣ።

መጽሐፈ አስቴር

1

1

በአርጤክስስም ዘመን እንዲህ ሆነ ይህም አርጤክስስ ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ
በመቶ ሀያ ሰባት አገሮች ላይ ነገሠ።

 

3

12

በመጀመሪያውም ወር ከወሩም በአሥራ ሦስተኛው ቀን የንጉሡ ጸሐፊዎች ተጠሩ ከህንድ ጀምሮ
እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ወዳሉ መቶ ሀያ ሰባት አገሮች፥ በየአገሩ ወዳሉ ሹማምትና አለቆች ወደ አሕዛብም ሁሉ ገዢዎች
እንደ ቋንቋቸው በንጉሡ በአርጤክስስ ቃል ሐማ እንዳዘዘ ተጻፈ፥ በንጉሡም ቀለበት ታተመ።

 

8

9

በዚያን ጊዜም ኒሳን በተባለው በመጀመሪያው ወር ከወሩም በሀያ ሦስተኛው ቀን የንጉሡ
ጸሐፊዎች ተጠሩ መርዶክዮስም ስለ አይሁድ እንዳዘዘው ሁሉ ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ በመቶ ሀያ ሰባቱ
አገሮች ላሉ ሹማምትና አለቆች አዛውንትም ለእያንዳንዱም አገር እንደ ጽሕፈቱ ለእያንዳንዱም ሕዝብ እንደ ቋንቋው
ለአይሁድም እንደ ጽሕፈታቸውና እንደ ቋንቋቸው ተጻፈ።

መጽሐፈ ኢዮብ

28

19

ኢትዮጵያ ቶጳዝዮን አይተካከላትም፥
በጥሩም ወርቅ አትገመትም።

መዝሙረ ዳዊት

68

31

መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።

 

72

9

በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።

 

74

14

አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ ኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።

 

87

4

የሚያውቁኝን ረዓብንና ባቢሎንን አስባቸዋለሁ እነሆ፥ ፍልስጥኤማውያን ጢሮስም ኢትዮጵያ ሕዝብ፥ እነዚህ በዚያ ተወለዱ።

ትንቢተ ኢሳይያስ

11

11

በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦርና ከግብጽ፥ ከጳትሮስና
ኢትዮጵያ ከኤላምና ከሰናዖር ከሐማትም፥ ከባሕርም ደሴቶች ይመልስ ዘንድ ጌታ እንደ ገና እጁን ይገልጣል።

 

18

1

ኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ ላለች፥ ክንፍ ያላቸው መርከቦች ላሉባት፥

 

20

3

እግዚአብሔርም አለ፦ ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብጽና ኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና
ለተአምራት ሊሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፥

 

20

4

እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና ኢትዮጵያ ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፥
ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፥ ለግብጽ ጕስቍልና ይነዳቸዋል።

 

20

5

እነርሱም ከተስፋቸው ኢትዮጵያ ከትምክሕታቸውም ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ ያፍሩማል

 

37

9

እርሱም፦ ኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊዋጋህ መጥቶአል የሚል ወሬ ሰማ። በሰማም ጊዜ ወደ
ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፥

 

43

3

እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥
ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።

 

45

14

እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። የግብጽ ድካምና ኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ
ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ ለአንተም ይሆናሉ እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል በፊትህም ያልፋሉ፥ ለአንተም እየሰገዱ።
በእውነት እግዚአብሔር በአንተ አለ፥ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም ብለው ይለምኑሃል።

ትንቢተ ኤርምያስ

13

23

በውኑ ኢትዮጵያ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? በዚያን
ጊዜ ክፋትን የለመዳችሁ እናንተ ደግሞ በጎ ለማድረግ ትችላላችሁ።

 

38

7

በንጉሡም ቤት የነበረው ጃንደረባ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ኤርምያስን በጕድጓዱ ውስጥ
እንዳኖሩት ሰማ። ንጉሡም በብንያም በር ተቀምጦ ነበር።

 

38

10

ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን አቤሜሌክም። ከአንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፥ ነቢዩም
ኤርምያስ ሳይሞት ከጕድጓድ አውጣው ብሎ አዘዘው።

 

38

12

ኢትዮጵያዊውም አቤሜሌክ ኤርምያስን፦ ይህን አሮጌ ጨርቅና እላቂውን ልብስ በብብትህ
ከገመዱ በታች አድርግ አለው ኤርምያስም እንዲሁ አደረገ።

 

39

16

ሂድ ኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው። የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ በዚያም ቀን
በፊትህ ይፈጸማል።


               

          

ትንቢተ ኤርምያስ

46

9

ፈረሶች ሆይ፥ ውጡ ሰረገሎችም ሆይ፥ ንጐዱ ጋሻም የሚያነግቡ ኢትዮጵያ የፋጥ ኃያላን፥
ቀስትንም ይዘው የሚስቡ የሉድ ኃያላን ይውጡ።

ትንቢተ ሕዝቅኤል

29

10

ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአንተና በወንዞችህ ላይ ነኝ፥ የግብጽንም ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ
ሴዌኔና እስከ ኢትዮጵያ ዳርቻ ድረስ ውድማና ባድማ አደርጋታለሁ።

 

30

4

ሰይፍ በግብጽ ላይ ይመጣል፥ ሁከትም ኢትዮጵያ ይሆናል የተገደሉትም በግብጽ ውስጥ
ይወድቃሉ፥ ብዛትዋንም ይወስዳሉ፥ መሠረትዋም ይፈርሳል።

 

30

5

ኢትዮጵያ ፉጥ ሉድም የተደባለቀም ሕዝብ ሁሉ ኩብም ቃል ኪዳንም የገባችው ምድር ልጆች
ከእነርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ።

 

30

9

በዚያ ቀን መልእክተኞች ተዘልለው የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማስፈራት ከፊቴ በመርከብ
ይወጣሉ እንደ ግብጽም ቀን ሁከት ይሆንባቸዋል እነሆ፥ ይመጣልና።

 

38

5

ፋርስንና ኢትዮጵያ ፉጥንም ከእነርሱ ጋር ጋሻና የራስ ቍርን የለበሱትን ሁሉ፥

ትንቢተ ዳንኤል

11

43

በወርቅና በብርም መዝገብ ላይ፥ በከበረችም በግብጽ ዕቃ ሁሉ ላይ ይሠለጥናል የልብያና
ኢትዮጵያ ሰዎችም ይከተሉታል።

ትንቢተ አሞጽ

9

7

የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል
እግዚአብሔር፦ እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?

ትንቢተ ናሆም

3

9

ኢትዮጵያ ግብጽ የማይቈጠር ኃይልዋ ነበሩ ፉጥና ልብያ ረዳቶችዋ ነበሩ።

ትንቢተ ዕንባቆም

3

7

ኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።

ትንቢተ ሶፎንያስ

2

12

እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ።

 

3

10

ኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱኝ፥ የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ፥ ቍርባኔን ያመጡልኛል።

የሐዋርያት ሥራ

8

27

ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ህንደኬ የተባለች ኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም

       ቅዱስ ሲኖዶስ
ቅዱ ሲኖዶስ1d
ቅዱስ ሲኖዶስ2
         ድረ መጻሕፍት
አማርኛ እንግሊዘኛ መዝገበ ቃላት
አማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ
ክብረ ነገሥት(እንግሊዘኛ)
መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት
ኪ/ወልድ መ. ቃላት
          ጠቃሚ

ዊኪፔድያ በአማርኛ
ጉግል በአማርኛ
መዝሙር ለመስማት
ፍትሐ ነገሥት (ዊኪፔድያ)
የሚነበብ
አለቃ አያሌው ታምሩ

ራድዮ ተዋህዶ
የበዓላትና የጽዋማት ቀን ማውጫ


Links

 
   



Unable to read the text?
 download  Nyala
 and copy in the  Directory
c:/windows/font/
 Unable to read the text? download  Nyala and copy in the directory  c:/windows/font/     
     
                                                                                                                   
 ቅድመ ገጽ cr መልእክት cr ተግባራት cr ጥቅሶች cr  ቃል  cr ድረገጾች